Wednesday, September 19, 2012


ፓርላማው ዓርብ አስቸኳይ ሰብሰባ ያካሂዳል-
ኃ/ማርያም ደሳለኝ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ                         

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማው)   የፊታችን አርብ አስቸኳይ ሰብሰባ ተጠርቷል ።
በስብሰባው ላይም አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርነት  ቃለ መሃላ  ይፈፅማሉ ተብሎ  ይጠበቃል ። ስብሰባው በቀጥታ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን እንደሚተላለፍም ተነግሯል።
የኢህአዴግ  ምክር ቤት በሰሞኑ መደበኛ  ስብሰባው አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን የግንባሩ  ሊቀመንበር አደርጎ  መምረጡ ይታወሳል ።

No comments:

Post a Comment

Zethiopia Event

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ እና ባለ ታሪኮች

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ  እና ባለ ታሪኮች
ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል (ለማንበብ ፎቶ ግራፉን ይጫኑ)