Monday, August 20, 2012

 
Meles Zenawi dies (aljazeera)

Ethiopian PM Meles dies from infection: state television

አቶ መለስ ዜናዊ አረፉ

አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለምፍ በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አስታውቋል። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለጊዜው ጠቅላይ ምኒስትር ሆነው እንደሚቆዩም መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

              
የሚኒስትሮች ምክር ቤት   የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትናንት ማምሻውን በህክምና ሲረዱ በነበሩበት  ሆስፒታል ማረፋቸውን  አስታውቋል

ምክር ቤቱ በመግለጫው ኢትዮጵያን ላለፉት 21 ዓመታት በከፍተኛ ብስለትና ብቃት ሲመሩ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስው ዜናዊ ካደረባቸው ህመም ለመፈወስ በውጭ አገር በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ጠቅሷል

ላለፉት ሁለት ወራት በህክምና ሲረዱና በጤናቸውም ላይ መሻሻል ሲታይ ከቆየ በኋላ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ  በተከሰተ ደንገተኛ  ኢንፌክሽን ህመማቸው አንደገና ተባብሶ ለአስቸኳይ የህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል  ገብተው ነበር
 
በህክምና ሙያተኞች ከፍተኛ እገዛ ቢደረግላቸውም በትናንትናት እለት ከምሽቱ 5 ሰዓት 40 ላይ በድንገት ማረፋቸውን ምክር ቤቱ ለአገራችን ህዝቦች በታላቅ ሀዘን ገልጿል

ኢትዮጵያንና  ህዝቦቿን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን  አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩን  መሪ እንደነበሩ  ነው ምክር ቤቱ የገለፀው 

አቶ መለስ ኢትዮጵያ በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ አቅጣጫ እንድትጓዝ ጥራት ያላቸው ፖሊሲዎችንና  ስትራቴጂዎችን  ነድፈው በብቁ አመራራቸው በገነቧቸው ድርጅቶችና መንግሰት አማካይነት ተግባራዊ ማድረግ የቻሉና በአገራችን  በመካሄድ ላይ ያለው ታላቅ አገራዊ የህዳሴ ጉዞ በሰመረ አቅጣጫ እንዲጓዝ ያደረጉ ታላቅ መሪ እንደነበሩ  ምክር ቤቱ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል

ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ለደቡብና ሰሜን ሱዳን ለሩዋንዳ ለቡሩንዲና ለላይቤሪያ ዘላቂ ሰላም አፍሪካውያን የማይዘነጉት አስተዋፅኦ እንድታበረክት አደርገዋል

 አቶ መለስ በዓለማችን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ስርዓት እንዲዋቀር የታዳጊ አገራት ድምፅ በመሆን በዓለም አደባባይ የተሟገቱና  ተቀባይነትን ያተረፉ ታላቅ መሪ ነበሩ

በዓለማችን  የተፈጥሮ ሀብት ሚዛን  እንዲጠበቅ በቃላቸው መሰረት ኢትዮጵያ የአረንጓዴው ልማት ሀሳባቸው ተግባራዊ ማሳያ እንድትሆንም አስችለዋል

በብስለታቸውና በአርቆ አሳቢነታቸው በአገራችን ቦግ ብሎ የበራውን የተስፋ ሻማ የለኮሱ ኢትዮጵያንና መላውን  የጥቁር ማህበረሰብ ያኮሩ መላው ዓለም ብቃታቸውን የመሰከረላቸው ታላቅ መሪ ነበሩ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመግለጫው ታላቁ መሪ  ዛሬ ከጎናችን ቢለዩም ትተውልን የሄዱት ህገመንግስታዊ ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አለና በፀና መሰረት ላይ የተገነባ በመሆኑ ምን ጊዜም በአቶ መለስ እንድንኮራ  በራሳችን ያለን መተማመን ከፍተኛ እንዲሆን በአገራችን በመካሄድ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ህዳሴ እውን የማድረግ ጉዞ መቼም ቢሆን  እንዳይቀለበስ ያረጋገጠ  ሆኗል ይላል

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሩህ አእምሮ ያፈለቃቸው መሰረታዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች  ተጠናክረው ተግባራዊ መሆን  ይቀጥላሉም ብሏል

በህገ መንግስቱ የተከበሩ የግልና የቡድን መብቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፍተውና ጎልብተው እንዲቀጠሉ ይደረጋል ያለው መግለጫው በአገራችን የተጀመረው የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ፈለግና ራዕይ ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል አረጋግጧል

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በመላው አፍሪካ በመጫወት ላይ ያለችው ገንቢ ሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ሚናም ተጠናክሮ ከመቀጠሉ በላይ እንደትናንቱ በአፍሪካ ህብረትና በዓለም አደባባይ የምትጫወተው ገንቢ ሚና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ባስቀመጡት ራእይና ፈለግ  በመመራት ተግባራዊነቱ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል ይደረጋልም ሲል ነው ምክር ቤቱ ያስታወቀው

የኢፌድሪ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀምበትን ሂደት በማስመልከት ቀጣይ መግለጫዎችን እንደሚያወጣ ገልጿል

በአገሪቱ  ህገ መንግስት መሰረት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ  የሚኒስትሮች ምክር ቤትን እየመሩ  ይቀጥላሉ ብሏል

1 comment:

  1. nefse yemar lemaletem eko tekekelegna kenun meglets neberebachew. any ways i'm glade to hear this good news.

    ReplyDelete

Zethiopia Event

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ እና ባለ ታሪኮች

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ  እና ባለ ታሪኮች
ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል (ለማንበብ ፎቶ ግራፉን ይጫኑ)