Wednesday, April 22, 2009


የዋሽንግተኑ አምባሳደር እናት የወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ቀብር ዛሬ ተፈጸመ

ባለፈው ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም በ93 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትና በ1908 ዓ.ም. የተወለዱት የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባልና የመጀመሪያዋ የሴት ዲፕሎማት ፣ ፣ አርበኛና ደራሲ፣የአምባሳደር ስንዱ ገብሩ የቀብራቸው ሥነሥርዓት ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።በዚህ የቀብር ሥነሥር ዓት ላይ ለመገኘት ከልጆቻቸው አንዱ የሆኑት በዋሽንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሳሙ ኤል አሰፋ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል። የወ/ሮ ስንዱ ባለቤት አቶ አሰፋ ለማ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የማእድን ሚኒስትር እንደነበሩ ይታወቃል።


No comments:

Post a Comment

Zethiopia Event

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ እና ባለ ታሪኮች

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ  እና ባለ ታሪኮች
ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል (ለማንበብ ፎቶ ግራፉን ይጫኑ)