Saturday, April 18, 2009

ፓትሪያርኩ ጥላሁን ቤት ለቅሶ ደረሱ- የአሜሪካ አምባሳደር መልክት ላኩ

አቡነ ጳውሎስ የጥላሁን ገሠሠን ቤተሰቦች አጽናኑ ሲል የመንግሥት ሚዲያዎች ዘገቡ።

ፓትሪያርኩ በአርቲስት ጥላሁን መኖሪያ ቤት ተገኝተው ቤተሰቦቹን ሲያጽናኑ ''ሞተ የሚባለው በምድር ላይ ምንም ዓይነት ተግባር ሳያከናውን ያለፈ ሰው ነው፡፡ ጥላሁን ግን በርካታ ስራዎችን ሰርቶ በማለፉ አልሞተም ''ማለታቸው ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ በአርቲስቱ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ኅዘን ገለጹ፡፡አምባሳደር ያማሞቶ በበኩላቸው አርቲስት የኢትዮጵያን ሙዚቃና ባህል ለዓለም ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ታላቅ ባለውለታ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኢትየጵያን መልካም ገጽታ ለቀረው ዓለም በማስተዋወቅ ረገድም አርቲስት ጥላሁን ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል፡፡

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

ዛሬ ሌሊቱን አስክሬኑ በተገኘበት በቅድስት ሥላሴ የጸሎት ሥነሥር ዓት የሚደረግለት ሲሆን አስክሬኑ ወደቤት ተመልሶ ከተወሰደ ይወሰዳል። ነገ ከቤት ተነስቶ በመስቀል አደባባይ ለሥነሥር ዓት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ አገር ፍቅር ቴ አትር ጎራ ካለበ ኋላ ወደ ማረፊያ ሥፍራ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚያመራ ተነግሯል። የዚህን ዓይነት የመሪ አቀባበር ሲደረግለት ጥላሁን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ይሆናል።

1 comment:

Zethiopia Event

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ እና ባለ ታሪኮች

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ  እና ባለ ታሪኮች
ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል (ለማንበብ ፎቶ ግራፉን ይጫኑ)