Saturday, March 7, 2009

ሕወሓት በቴሌኮሙኒከሽንና ፖስታ ድርጅትም ተከበረ

አዲስ አበባ የቴሌኮሙኒኬሽንና የፖስታ ድርጅት የሚገኙ 700 የወያኔ ሓርነት ትግራይ አባላትና ደጋፊዎች የድርጅታቸውን 34ኛ የልደት በዓል ማክበራቸው ተዘግቧል። የካቲት 22/2001 በተካሄደው በዚሁ በዓል ላይ የደህንነት ከፍተኛ ባለሥልጣና የነበሩትና የወያኔ ሓርነት ትግራይ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የቴሊኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል በእንግድነት መገኘታቸው ተዘግቧል። “መንግስታዊው ቴሌኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን እያለ ሌላ ተደራቢ ተቋም ማቋቋም ለምን ያስፈልጋል?” በሚል የሚያወዛግበውን፣ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና የኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂው ልማት ኤጄንሲ ዳይሬክተር በመሆን፣ ዘርፉን በኃላፊነት የሚመሩት አቶ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል “የህወሓት ትግል ከደርግ መደምሰስ በኋላም ህያው ታሪክ ሆኖ በፀረ ድህነት ትግልም ላይ ቀጥሏል” ማለታቸው ተዘግቧል። በትግሉ ለተሰው ሰማእታትም የሕሊና ፀሎት መደረጉ የተነገረ ሲሆን 34 ሻማዎች መብራታቸውና አዝናኝ ዝግጅቶች መደረጋቸውም ተዘግቧል። በአዲስ አበባና የተለያዩ ክፍለ ከተማዎችና በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የወያኔ ሓርነት ትግራይ የልደት በዓል መከበሩ በኢትዮጵያ የመንግሥት ዜና ማሰራጫዎች ሲነገር ሰንብቷል። በተያያዘ ዜና ትግራይ ውስጥ በአክሱም አዲአቡን ከተማ በ8ሚሊዮን ብር በትግሉ ለወደቁ የወያኔ ታጋዮች ሐውልት ለማቆም አቶ ስብሐት ነጋና የትግራይ ፕሬዘዳንት አቶ ፀጋይ በርኸ የመሠረት ድንጋይ ማኖራቸው ተዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

Zethiopia Event

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ እና ባለ ታሪኮች

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ  እና ባለ ታሪኮች
ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል (ለማንበብ ፎቶ ግራፉን ይጫኑ)