Tuesday, March 10, 2009


Ethiopia ONLF rebels 'seize town'
የኦጋዴን አማጽያን አንድ ከተማ ተቆጣጠርን አሉ

በምስራቅ ኢትዮጵያ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የኦጋዴን ነጻ አውጪ አማጽያን ሙስታሂል የተባለችውን ከተማ መቆጣጠራቸውንና ዋርዴርና ቀላፎ የተባሉትን ከተሞች ለመቆጣጠር እየተዋጉ መሆኑን መግለጻቸውን ቢቢሲ በማርች 9/2009 ዘገባው አመልክቷል። ኦጋዴን እየተባለ የሚታወቀውን አካባቢ ከምስራቅ ኢትዮጵያ ለመገንጠል ይንቀሳቀሳሉ የሚባሉት እነዚሁ አማጽያን 80 የሚደርሱ የኢህ አዴግ መንግሥት ወታደሮችን መግደላቸውን መግለጻቸውም ተዘግቧል። የኢህአዴግ መንግሥት በበኩሉ ዘገባውን አስተባብሎ እንዲያውም በተቃራኒው አማጽያኑ በመሸሽ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል። የኦጋዴን ነጻ አውጪ ድርጅት በ1984 የተቋቋመ ሲሆን በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የሶማልኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ን ከኢትዮጵያ አስተዳደር ነጻ ለማውጣት የሚታገል ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment

Zethiopia Event

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ እና ባለ ታሪኮች

ከዘኢትዮጵያ ታሪክ  እና ባለ ታሪኮች
ይህን ቅርስ በአደራ ጠብቀውና ተከላክለው ያቆዩት ብ/ር ጄነራል ፍሬሰንበት አምዴ ነበሩ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ላለፉት 30 ዓመታት ቤተመንግሥትን በዋናነት ሲያስተዳድሩ ከነበሩት ጄነራል ፍሬሰንበት ህይወት ጋር አብሮ የሚጻፍ ብዙ ታሪክ አለ። ለምሳሌ እነዚህ ይገኙበታል (ለማንበብ ፎቶ ግራፉን ይጫኑ)